Blog

Why We Need a community

ጉዳዩ የጋራ መረዳጃ ማህበር አስፈላጊነትና ያስገኛቸው ጥቅሞች

የኢትዮጵያውያን የጋራ መረዳጃ ማሕበር በአጠቃላይ በሰሜን አሜሪካም ይሁን በሌሎች አገሮች የሚቋቋሙበት ምክንያት
ለተመሳሳይ ዓላማ ነው ለማለት ይቻላል። ይኸውም እኛ ኢትዮጵያውያን በስደት የምንኖረው ተወልደን ካደግንበት አገራችን
ውጪ በመሆኑ በሁሉም መስክ እጅግ የተለያዩ ሁኔታችግሮች የሚያጋጥሙን ስለሆነ ይህንን ሁኔታ ለመቅረፍ በያለንበት ትንንሽ
ኢትዮጵያን ፈጥረን በአኗኗራችን ላይ የሚገጥሙንን ልዩ ልዩ ውጣ ውረዶችን በጋራ ተረዳድተን ለመቋቋም ሲሆን በተለይም
የአሜሪካን አገር ሥርዓትም ተደራጅቶ ራሱን ለሚረዳ ብዙ ጥቅሞችን በመስጠት ስለሚያበረታታ ይኽው ማድረግ ብልሕነት
በመሆኑ ነው። የጋራ መረዳጃ ማሕበር የሚያስፈልግበት ዋና ዋና ምክንያቶች

1ኛ/ ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ለአንድ ሰው ሸክሙ እንደሚባለው በተናጠል ለመፈጸም ከአቅም በላይ የሆኑ ማንኛቸውም
ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቋቋም ማህበር አቁቋሞ በጋራ መቆም ወሳኝ በመሆኑ የዳላስ ቴካሳስ ኢትዮጵያውያንም
ይኸው ጉዳይ በተግባር አውለው ፍሬውን መቋደስ ከጀመሩ ብዙ ዘመናት አስቆጥረዋል። ለምሳሌ ያሕል ድንገተኛ ሞት አንዱ
ኢትዮጵያዊ ቤተስብ ውስጥ ቢከሰት፤ ከአንድ ቤተሰብ አቅም በላይ ሆኖ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚያስፈልግ ከመሆኑ ባሻገር የሰው ሃይል
እርዳታም ጭምር የሚጠይቅ ጉዳይ ስለሚሆን በኢትዮጵያችን እንደሚደረገው ተመሳሳይ የሆነ ዕድር ተቋቋሞ ከዚያ በፊት በልመና ይከናወን
የነበርውን አስጸያፊ ችግር ማስቀረት ትችሏል። ከዚህም ባሻገር ዜጎች በመንግስት አካላት ሲበደሉ፤ መብተቸው ሲነፈጉ፤ በወንበዴዮች ሲገደሉ ያለአግባብ ሲታሰሩና ያለበቂ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ሲነፈጋቸው የተባበረ ክንድ አስፈላጊነቱ ስለማያጠያይቅ በቅድሚያ ተደራጅቶ በመቆየት ችግሮችን ሲፈታ ቆይቷል።

2ኛ/ አሜሪካን አገር ከዓለም ዙርያ የተሰባሰቡ የተለያዩ አገር ሰዎች መኖሪያ ሲሆን ኢትዮያውያንም የዚሁ ህብረት አባላት ናቸው። ከዚሁ በመነጨ ልጆቻችን በዜግነት አሚሪካያን በመልክና በደም ግንኙነት ኢትዮጵያውያን ናቸው በተጨማሪም በትምህርትና በሥራ ምክንያት ከቤታቸው ውጪ በሚውሉበት ጊዜ የሚያጤኑትና እቤት ሲገቡ የሚያጋጥማቸውን ሁሉ በአዕምሮአቸው እየተመላለሰ ለሚያስቸግራቸውን የማንነት ጥያቄ ተጨባጭና የሚዳሰስ ጥሩ መልስ ካላገኙ በእድገታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ሊፈጥር ይችላል። በመሆኑም በእድሜ በጾታና በመልክ ተመሳሳያቸው የሆኑትን የራሳቸው ወገኖች አግኝተው ሲተዋወቁ ሃሳብ ለሃሳብ ሲለዋወጡና የወላጆቻቸውን ታሪክ፤ ባሕል፤ ወግና እምነት በሕብረት ሲያጣጥሙት ትልቅ እርካታና የራስ መተማመን ይፈጥርላቸዋል ለማለት ይቻላል። ስለሆነም በኢትዮጵያውያን የጋራ መረዳጃ ማህበር አማካይነት እንደሌሎች ኮሚኒቲዮች የተደራጀና ደረጃውን የጠበቀ ወቅታዊ የመገናኛ በዓል እንደአስፈላጊነቱ በመንፈቅና በአመት አንድ ጌዜ ለማዘጋጀት አንድ የተደራጀ ሃይል በማስፈለጉ ሲሆን ፤ ከዚህ አኳያ በየዓመቱ በመስከረም ወር የሚከበረ የኢትዮጵያውያን በዓል ጥሩ ምሳሌ ነው ለማለት ይቻላል።

3ኛ/ በተለያዩ ጊዚያት ባለንበት አሜሪካ ይሁን ባዓለም ዙርያ በወገኖቻችን ላይ ሰው ሰራሽም ይሁን ተፈጥሮአዊ ችገሮች ሲከሰቱ በተደራጀ መልክ ተመጣጣኝ የሆነና አፋጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ የሚያጠያይቅ አይደለም። እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች በሕግ አዋቂ ወይንም በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና በባለሙያ ወዘተ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላል። ወይንም በሕብረት ቆሞ ተጽእኖ መፍጠር የሚያሻው ሥራ ሊሆን ይችላል ፤ በተለያዩ ጊዜያት በአሰሪዮቻቸው ባሪያ የተደረጉትን ኢትዮጵያውያን ነጻ ለማውጣት የተደረጉ እንቅስቃሴዮች፤ በሳውዲ አሬቢያ ፤ በየመን፤ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ችግር ለመፍታት የተደረገው የጋራ ንቅናቄ አይነት ሊሆን ይችላል ወዘተ። ስለሆነም የዚህ አይነት አቢይ ጉዳዮች ደግሞ ውድ የተባበረ እጅና የሰው ሃይል የሚጠይቁ ስለሆኑ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በመሰለ አስተባባሪ ኃይል ቀደም ብሎ መደራጅትና መዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

4ኛ/ በአካባቢያችን የሚገኙ የዕምነት ተቋማትና የኢትዮጵያውያን የንግድ ድርጅቶች መሰረታዊ ንብረትነታቸው የሕዝባችን በመሆናቸው ለጋራ መረዳጃ ማሕበራችንና የዜጎቻችን ትልቅ ሃይል ከመሆናቸው በተጨማሪ ወገኖቻችን በየዕለቱ ለተለያዩ ፍላጎታቸው የሚጎበኙዋቸው ናቸው። በመሆኑም እነሱንም በማስተባበርና የሙያ ትምህርታቸው እንዲያጎለብቱ በመርዳት ለወገኖቻችን ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማደረግ ባሻገር ቅርበት ፈጥሮ በጋራና በህብረት በመስራት ማሕበራችን የሚፈለግበትን እንዲሰጥና የሚያሻውንም እንዲያገኝ ተገቢውን ሁሉ ማደረግ በማስፈለጉ ነው።

የሚከበር የኢትዮጵያውያን ዕለት በዓል መስርተን እርስ በእርሳችን ከመተዋወቅ ባሻገር እኛና ልጆቻችን
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን አቢይ ስራዎች በድርጅት መልክ ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ መረዳጃ ማህበር ከብዙ አመተት በፊት ጀምሮ ተቋቋሞ ዜጎቻችንን በጋራና በህብረት በማንቀሳቀስ ጥሩ ውጤት ያስገኘ ሲሆን ሁላችንም የዚህ ፍሬ ተጠቃሚዮች ሆነናል ለማለት ይቻላል።

እንተባበር
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
በጥረታችን እናሸንፋለን

temp-post-image

በውጤታችን እንረካለን

Mutual Assistance Association for the Ethiopian Community

9858 Plano Rd,

Suite #110,

Dallas, TX 75238

Phone. 214-321-9992

Email. maaecdfw@gmail.com